ቀዳሚ ገጽ

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሐመረ ብርሃን ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ ቤተ ክርስቲያን

ነስሑ እስመ ቀርበት መንግሥተ ሰማያት ማቴ. ፫፥፪፣ ማር. ፩፥፪፣ ሉቃ. ፫፥፫

መንግሥተ ሰማያት በልጅነት፤ ልጅነት በሃይማኖት ልትሰጥ ቀርባለችና እመኑ፤ ንስሐ ግቡ

ውድ አንባቢያን በቅድሚያ በልዑል እግዚአብሔር ፈቃድ በመጥምቀ መለኮት ቅዱስዮሐንስ ስም በአሜሪካ ሀገር የመጀመሪያ ወደ ሆነው ወደ ሐመረ ብርሃን ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ ቤተ ክርስቲያን ድረ ገጽ እንኳን ደህና መጡ። አገልግሎቱን በእውን ለማየትና ለመገልገል የቻልነውንም እንኳን ለዚህ አበቃን እላለሁ።

መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ

መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ቅዱስ ገብርኤልና አባቱ ዘካርያስ ትንቢት የተናገሩለት፤ ከሕፃንነቱ ጀምሮ እግዚአብሔርን ያገለገለ፤ በፍጹም ልቡ ዓለምን የናቀ፤ ከተድላዋና ከደስታዋም የተለየ፤ አምላክን ለማጥመቅ የታደለ ሐዋርያ፣ መምህር፣ ሰማዕት፣ ባሕታዊ፣ ነቢይ፣ ጻድቅ ነው፡፡

ሊቁም ከመላእክት፣ ከነቢያት፣ ከካህናት፣ ከሐዋርያት መካከል እንደርሱ መለኮትን ለማጥመቅ የተመረጠ አለመኖሩን በመጥቀስ ‹‹… ዮሐንስ ከማከ ሶበ ፈተዉ ወጽሕቁ፤ እሳተነዳዴ ኢተክህሎሙ ያጥምቁ፤ ራጉኤል በትጋሁ ወኢዮብ በጽድቁ፤ … ዮሐንስ ሆይ! ራጉኤል በትጋቱ፣ ኢዮብምበጽድቁ ቢመኙም ኾነ ቢጨነቁ እንደ አንተ የሚነድ እሳትን (መለኮትን) ሊያጠምቁ አልተቻላቸውም›› ሲል ታላቅነቱን መስክሮለታል (መልክአ ዮሐንስ መጥምቅ፣ ለአዕይንቲከ)፡፡

ዮሐንስ ማለት ‹‹እግዚአብሔር ጸጋ ነው›› ማለት ነው፡፡ ቅዱስ ወንጌልም መጥምቀ መለኮት ዮሐንስን ፍሥሐ ወሐሴት (ተድላና ደስታ) ይለዋል፤ ወላጆቹ በእርሱ መወለድ ተደስተዋልና (ሉቃ. ፩፥፲፬)፡፡ በቅዱስ ሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ አንድ፣ ከቍጥር አንድ ጀምሮ እንደ ተገለጸው ካህኑ ዘካርያስ እና ሚስቱ ቅድስት ኤልሳቤጥ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ዅሉ በመፈጸም ያለ ነቀፋ የሚኖሩ ጻድቃን ነበሩ፡፡ ኤልሳቤጥም መካን ነበረችና ልጅ አልነበራቸውም፡፡ ልጅ ይሰጣቸው ዘንድም እግዚአብሔርን ዘወትር ይማጸኑት ነበር፡፡

 ስለእኛ 

የሐመረ ብርሃን ቅዱስ ዮሐንስ ቤተ ክርስቲያን እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ያነሳሳቸው ካህናት፣ ምዕመናንና ምዕመናት ተሰባስበው ሲመካከሩ ከቆዩ በኋላ ቤተ ክርስቲያን ለመትከል በመወሰናቸው በቀኖና ቤተ ክርስቲያን መሠረት በብፁዕ አቡነ ፋኑኤል በዚያን ጊዜ የዲሲና ካሊፎርኒያ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፈቃድ በ፳፻፱ ዓ.ም (2017 እ.አ.ዘ) የተተከለ ነው። ቤተ ክርስቲያኑ የተተከለው በሜሪላንድ ግዛት በሞንትጎሞሪ ክልል ማለትም በራክቪል፣ ጌተርስበርግ፣ ኦልኒ፣ ጀርመን ታውን፣ ክላርክስበርግ፣ ፖቶማክ፣ ሲልቨርስፕሪንግ፣ ወዘተ. አካባቢ የሚገኙ ምዕመናን በቦታ ርቀት ምክንያት ወደ ሌሎች አብያተ ክርስቲያናት ለመሄድ ባለመቻላቸው መንፈሳዊ አገልግሎት እንዲያገኙና የምሥጢራት ተሳታፊ እንዲሆኑ ለማድረግ ነው።

ፕሮጀክቶች

ይህ በአሁኑ ሰዓት በግንባታ ላይ የሚገኘው የሐመረ ብርሃን ቅዱስ ዮሐንስ ቤተ ክርስቲያን  ፕሮጀክት አካል በአይነቱ ለየት ያለ ዘመናዊ የሆነ የቤተ ክርስቲያን ህንጻ ነው፡፡ ይህ ህንፃ በይዘቱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን የአሰራር ይዘትና ውስጣዊ ውበት የጠበቀ ሲሆን በውስጡ ባለሁለት መቅደስ ሆኖ የሚሰራ በእያንዳንዱ መቅደስ ቢያንስ እስከ አምስት መቶ ም ዕመናንን በአንድ ጊዜ ሊይዝ የሚችል ነው፡፡ 

በመጀመሪያው ወለል ላይ አንደኛው መቅደስ የሚሰራ ሲሆን በሁለተኛው ወለል ላይ ደግሞ ሌላ ሁለተኛው መቅደስ ይሰራል፡፡ ህንፃው ከአየር ላይ ሲታይ በመስቀል ቅርጽ የተቀረጸ ሲሆን በቅርጸ መዋቅሩና በጠቅላላ በውጭና በውስጥ የሚቀረጹት ምስሎችና መልእክቶች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስን አስተምህሮት በሚያንጸባርቅ መንገዱ የሚሰሩ ሲሆን ምዕመኑ በአጸደ ቤተ ክርስቲያኑ ቅጽር ግቢ ውስጥ በሚኖርበት ጊዜ ጠቅላላ ልቦናውንና ውስጠቱን ከፈጣሪው ጋር በሚያስተሳስር ልዩ መስህብ ይኖረው ዘንድ ታቅዶ የተወጠነ ነው፡፡ ይህ ህንጻ አልቆ በሥራ ላይ ሲውል በጠቅላላው በህንፃ መዋቅርነቱም ሆነ በአንድ ጊዜ ሁለት አገልግሎት ያለባቸው ሁለት መቅደሶችን በውስጡ በመያዙ፣ ብሎም በውጫዊና በውስጣዊ ይዘቱ በአይነቱ ሌላ ተመሳሳይና ወደር የሌለው ህንጻ ቤተ ክርስቲያን እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡

የቤተ ክርስቲያን ህንጻ

This is a label

Lorem ipsum

Lorem ipsum dolor sit amet consect voluptate repell endus kilo gram magni illo ea animi.

This is a label

Lorem ipsum

Lorem ipsum dolor sit amet consect voluptate repell endus kilo gram magni illo ea animi.

This is a label

Lorem ipsum

Lorem ipsum dolor sit amet consect voluptate repell endus kilo gram magni illo ea animi.

This is a label

Lorem ipsum

Lorem ipsum dolor sit amet consect voluptate repell endus kilo gram magni illo ea animi.

ትምህርት

ቅበላ የኅሊና ዝግጅት ወይስ?

ይህንን ጽሑፍ በ2007ዓ.ም በwww.eotcmk.org ለንባብ ያበቃሁት ሲሆን ዛሬም ሰሞነኛ ሆኖ መጥቷልና መልካም ንባብ። ቅበላ ማለት የጾም ዋዜማ ፣ጾም ከመግባቱ በፊት ቀደም ብሎ ያለው ቀን ወይም ሰሞን

የጥምቀት ከተራ በዓል አከባበር የትመጣ

ይህን ጽሑፍ ጥር 9 ቀን 2006 ዓ.ም በማኅበረቅዱሳን ድረ-ገጽ/ www.eotcmk.org አውጥቼው የነበረ ሲሆን አሁን መጠነኛ ማስተካከያ ተደርጎበታል፡፡ ከተራ ከበበ ካለው የግእዝ ግሥ የወጣ ነው፡፡ ፍችው ውኃ

ጥምቀት

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ††† <<< በዓለ ኤጲፋንያ >>> ††† “ኤጲፋንያ” የሚለው ቃል ከግሪክ (ጽርዕ) ልሳን የተወሰደ ሲሆን በቁሙ “አስተርእዮ:

ልለግስ

ምጽዋት ለመስጠት

ምጽዋት ለመስጠት ምጽዋት ለመስጠት ምጽዋት ለመስጠት ምጽዋት ለመስጠት
ምጽዋት ይስጡ

ስለት ለማስገባት

ስለት ለማስገባት ስለት ለማስገባት ስለት ለማስገባት ስለት ለማስገባት
ስለት ያስገቡ

አስራት ለማስገባት

አስራት ለማስገባት አስራት ለማስገባት አስራት ለማስገባት አስራት ለማስገባት
አስራት ያስገቡ

ወርኃዊ የአባልነት ክፍያ

ወርኃዊ የአባልነት ክፍያ ወርኃዊ የአባልነት ክፍያ ወርኃዊ የአባልነት ክፍያ ወርኃዊ የአባልነት ክፍያ
ወርኃዊ የአባልነት ክፍያ ይክፈሉ